image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ፅ/ቤት በመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ተቋማዊ ሪፎርሙ ያመጣቸውን ውጤቶች እና ተግዳሮቶች ከህብረት ስራ ማህበራት እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

ነሀሴ 24, 2017
በውይይቱም ላይ የመልካም አስተዳደር ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እና የመጡ ውጤቶች እንዲሁም በተቋማዊ ሪፎርም የመጡ ውጤቶች እና ተግዳሮቾች የህብረት ስራ ማህበራት አመራሮች ፣ ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች በተገኙበት በጥልቀት በመወያዩት በቀጣይ በዓላት የሚሆን ግብዓት በማስገባትና ለሸማቹ ለማሰራጨት እየተደረገ ያለውን ዝግጅት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል። ሁሉም ማህበራት የተቋቋሙበትን ዋና አላማ መነሻ በማድረግ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው የጋራ መግባባት መፍጠር ተችሏል ያሉት አቶ ባዬ በተጨማሪም በውይይቱም በቀጣይ የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የአገልግሎት አሠጣጥ መማክርት ጉባኤ አባላትን በመምረጥ የተጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርሙን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በውይይቱ መግባባት ተችሏል በቀጣይ የህብረት ስራ ማህበራት በህብረት ሰርቶ በህብረት ማደግ የሚያስችል አቅም መፍጠር የሚያስችል ተቋማዊ ለውጥ በተግባር እያረጋገጥን መሄድ አለብን በተለይም የህብረተሠቡን ፍላጎት መሠረት ያደረገ አቅርቦት እና ፍላጎትን የሚጣጥም ተግባራትን ማከናወን ይገባል ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች