image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ 21 ሺህ 971 ለሚሆኑ በእንስሳት እርባታ ለተሰማሩ አርቢዎች የእንስሳት መኖ የማቅረብ ስራ ተከናወነ።

መጋቢት 5, 2017
የክ/ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ከህብረት ስራ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ትስስር ለተፈጠረላቸው አርቢዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የእንስሳት መኖ አቅርበዋል። የክ/ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው እንደተናገሩት መኖውን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ መቻሉ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ይጨምራል ብለዋል። በሌማት ቱሩፋት ስራ የከተማዋን ነዋሪዎች ከሸማችነት ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩ ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በዚህም አብዛኛው የከተማው ነዋሪዎች ባላቸው ክፍት ቦታ እንስሳት በማርባት ከራሳቸው አልፈው ለገብያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። አርቢዎች ምርታቸውን በስፋት እንዲያመርቱ ለማስቻል ክ/ከተማው የእንስሳት መኖ አቅርቦት በፋት እያቀረበ ይገኛል በዚህም በዛሬው ዕለት በያዋጣናል እና በትግል ፍሬ ሸማች ህብረት ስራ ማህበር አማካኝነት መኖ እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ገልፀዋል። መኖ እየቀረበ የሚገኘውም ሌላ ቦታ ከሚሸጠው ከ8 መቶ እስከ 1 ሺህ ብር የዋጋ ቅናሽ እንዳለውም ተጠቁሟል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች