image
image
image
image
image

2ኛው ዙር የህብረት ስራ ማህበራት ሪፎርም ትግበራ ውጤታማ መሆኑን የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የምክር ቤት አመራሮችና አባላት ገለፁ።

ግንቦት 21, 2017
የምክር ቤቱ አመራርና አባላት በልደታ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት በ2ኛው ዙር እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ስራዎችን ጎብኝተዋል። የምክር ቤት አመራርና አባላት በህብረት ስራ ማህበራት እየተከናወነ ያለው ሪፎርም የረጅም ጊዜ የማህበረሰቡን ጥያቄዎች የመለሰ ነው ብለዋል። የህ/ሰራ ማህበራት 2ኛው ዙሪ የሪፎርም ትግበራ ውጤታማና ከዚህ በፊት የነበረውን የተንቀራፈፈ አሰራርና የግብዓት ብክነት ያስቀረ መሆኑን የገለፁት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ባየ ባይሌ ትግበራው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። ኃላፊው አክለውም በሪፎርሙ የተተገበሩ ስራዎች ደረጃቸውን የጠበቁና ሸማቹ ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልፀው በርካታ የስራ እድል እንደተፈጠረባቸውም አብራርተዋል። ሱፐር ማርኬቶች፣ የመዝናኛ ክበቦች፣ የእንጀራ መጋገሪያ እና የተለያዩ ካፌዎች የሪፎርሙ ውጤቶች መሆናቸውን ተገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች