የተቋሙ ስልጣን ፤ ተግባርና ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች
2. የኅብረት ስራ ዕሴቶች፣ መርሆዎች፣ አደረጃጀትና ጠቀሜታ በሕብረተሰቡና በትምህርት ተቋማት ይበልጥ እንዲታወቁ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን ያከናወናል፣
6. የኅብረት ሥራ ማህበራት እና የጋራ ሕንጻ ቤት ባለቤቶች ማህበር በአካባቢ ልማትና በማህበራዊ አገልግሎት እንዲሳተፉ አሰፈላጊውን ደጋፍና ክትትል ያደርጋል፣
7. የኅብረት ሥራ ማኅበራት ባንክ እና ኢንሹራንስ ስለሚቋቋሙበት ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፣ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፣
16. የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ይሰጣል፣ ኅብረት ስራ ማህበራትን ይመዝናል፣ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ይሰጣል፣ ይሰርዛል ፣
18. ተጠሪነቱ ለኤጀንሲው የሆነ የኅብረት ሥራ ማኅበር አማካሪ ምክር ቤት ያቋቁሟል ተግባርእና ኃላፊነቱን በቢሮው በሚወጣ መመሪያ የሚወስን ይሆናል ፡፡
20. በክፍለ ከተማ ወይም ወረዳ ለሚደራጁ ፅ/ቤቶችና የህብረት ስራ ማህበራት የቴክኒክና የሙያ ዕገዛ ያደርጋል፡፡
21. የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከስሳል፣ ይከሳል፣፡