image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ለባለሙያዎችና ለባለድርሻ አካላት በሂሳብ አያያዝ በአጫጭር ጥናትና ፣ በቢዝነስ ፕላን ዙሪያ ስልጠና ሰጠ::

ታህሳስ 4, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ የህብረት ስራ ማህበር ጽ/ቤት ሀላፊ እንደተናገሩት ጽ/ቤቱ በቅርቡ ሪፎርም ያደረገ ተቋም እንደ መሆኑ ስልጠና በመስጠት ሸማች ማህበሩ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና የተሻለ የሒሳብ አያያዝ ላይ ግንዛቤ መፍጠር መቻሉ እንደ ጠንካራ ጎን የሚወሰድ ነው በማለት ሰልጣኞች የሂሳብ አያያዝና ላይ የተሻለ ግንዛቤና ክህሎት ኖሯቸው በተሰማሩበት የስራ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛል በማለት ገልፀዋል። አቶ ባዬ አክለው ስልጠናው የተሻለ ክህሎትና አቅም እንደሚፈጥር እና ስራዎችን አንድ ደረጃ ከፍ አድርገን እንድንሰራ የሚያደርግ ነው በማለት ሰልጣኞችም ከስልጠናው በኋላ የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ሊወጡ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል ወደ ተግባር መለወጥ ይጠበቅባችኋል በማለት ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች