image
image
image
image
image

"ጠንካራ ተቋማዊ ሪፎርም ለተቋም ግንባታ መሰረት ነው'' በሚል መሪ ቃል ለጽ/ቤት አመራሮች ፣ለባለሙያዎች እና ለሸማች ማህበራት አመራሮች ስልጠና ተሰጠ ።

ጥቅምት 11, 2017
ስልጠናውን የሚሰጠው የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ማህበር ሲሆን ጽ/ቤቱ በህብረት ስራ ማህበራት መመሪያና ደንብ ቁጥር 170 እና 171/2016 መሰረት በማድረግ እየሰጠ ያለው። የክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባዬ ባይሌ የስልጠናውን ዓላማ ሲገልፁ በሸማች ሪፎርም የተጀመረውን ትግበራ ውጤታማ እንዲሆንና ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች፣ባለሙያዎችና ሸማች ማህበራት በመመሪያና ደንብ ላይ ያላቸው ግንዛቤ ተመጣጣኝ እንዲሆን ለማስቻል ነው ብለዋል። አቶ ባዬ አያይዘው እንደገለፁት ተቋማችን የህዝብ እንደመሆኑ መጠን አገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍ፣አሰራሩን ለማሻሻል በየጊዜው የለውጥ ስራዎች እየሰራን እንገኛለን ያሉ ሲሆን ከእዚህ ስልጠና በኋላም የህብረተሰቡን ፍትሀዊ የሆነ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣የመልካም አስተዳደር ችግርን መቅረፍ፣ የህብረተሰቡን ፍላጎትና አቅርቦት አመጣጥኖ በማቅረብ የኑሮ ውድነትን ማቅለል፣ ማንኛውም በህብረት ስራ ላይ ተጠቃሚ የሚሆን አካል ህግና መብቱን አዉቆ በስርዓት እንዲገለገል ውጤት ይጠበቃል ዓላማው እንዲሳካም ስልጠናውን ተግባራዊ ማድረግና በጋራ መስራት አለብን ብለዋል። ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለ4 ቀን እንደሚቆይና የሚሰጠውን ስልጠና በጥብቅ ዲሲፒል ተከታትሎ ማጠናቀቅ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች