image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ፅ/ቤት ለመጭው አዲስ አመት በአልን ምክንያት በማድረግ ለበአሉ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ምርቶችን በሸማች የህብረት ስራ ማህበራት በኩል በቂ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገለፀ።

ነሀሴ 29, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ የህብረት ስራ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ባዬ ለመጪው አዲስ አመት ለበአሉ የሚያስፈልጉ የግብርናና ፣የኢንዱስትሪ ምርቶችን እንዲሁም የእንስሣት ተዋፅኦ ምርቶችን በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ በሸማች የህብረት ስራ ማህበራት በኩል በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል ። በሸማች ማህበራት በመጋዘኖች የመሸጫ ሱቆች እና በእሁድ ገቢያዎች እንዲሁም በአሉን ታሣቢ በማድረግ በ10 ወረዳዎች ባዛር በማዘጋጀት ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የህብረት ስራ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ባዬገልፀዋል። በአሉንም ምክንያት በማድረግ በሁሉም የሸማች ማህበራት መጋዝኖች እና የመሸጫ ሱቆች ላይ በቂ የዘይት ምርቶች በማስገባት ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቱ እንደሚቀርብ ገልፀዋል ። የበአላት የፍጆታ ምርት አቅርቦቱ በቀጣይ ቀናቶችም በተጠናከረ አግባብ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንደሚቀርብ የገለፁት አቶ ባዬ አያይዘው ለመጪዎቹ በአላት ለፋጆታ የሚውሉ ግብዓቶችን ከአምራቾች እና ምርት አቅራቢ ዪኔኖች ጋር ጠንካራ የገቢያ ትስስር በመፍጠር ለህብረተሰቡ አስፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑን ሃላፊውም ተናግረዋል ። በዛሬው እለትም ፈሳሽ ዛይት በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ወደ ማህበራቱ የመጋዝኖች እና መሸጫ ሱቆች መግባታቸው ገልጿል። መጪዎቹን በዓል ምክንያት በማድረግ በሁሉም የሸማች ሱቆችና ወፍጮ ቤቶች ፤ ጤፍን ጨምሮ ሀሉንም አይነት የሰብል ምርቶች እንዲሁም እሴት የተጨመረባቸው ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ይቀርባሉ ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች