በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2016 ዓ.ም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት በወጣ አዋጅ ቁጥር 84/2016 መሰረት የህብረት ስራ ፅ/ቤት እንደገና የተቋቋመ ሲሆን ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡
ስለሆነም ፅ/ቤቱ የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ አገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የፅ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች አገልግሎቶቹን በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ (standard) ማግኘት እንደሚገባቸው አውቀው በአገልግሎት አሠጣጥ ላይ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው አስተያየት፤ ጥቆማና ግብዓት የሚሰጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ይህ የዜጎች ስምምነት ቻርተር እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡
የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ
-
ተገልጋዮች ኮሚሽኑ በሚሰጣቸውአገልግሎቶች ተጠቃሚ ሆነውእርካታቸውን በሚያሻሽል መልኩ አገልግሎት ለመስጠት፤
-
ተገልጋዮችን በማሳተፍ ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት፤፣
- ተገልጋዮች በኮሚሽኑ አገልግሎት አሠጣጥ ላይ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው አስተያየት፤ ጥቆማና ግብዓት የሚሰጡበትን ምቹ ሁኔታ ለማመቻቸት፤
- ዜጎች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ለማሳወቅ፤
- የዜጎችን የመረጃ ማግኘት መብት ለማረጋገጥ እና
- ኮሚሽኑ ለዜጎች ግልፅ፤ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለበትና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡
የፅ/ቤቱ ተገልጋዩች
-
በኅብረት ሥራ ማህበራት ለመደራጀት ፍላጎት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች
- በተለያየ አይነትና ደረጃ የተደራጁ የኅብረት ስራ ማህበራት፣
- የኅብረት ሥራ ማህበራት አባላት
- የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የተገልጋዮች መብት
- ምንም ልዩነት ሳይደረግበት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የመሆን፣
- ማንኛውም ተገልጋይ በአገልግሎቱ አሰጣጥና በአገልግሎት ሰጪው ቡድን/ሠራተኛ ላይ ያለውን አስተያየትና ቅሬታ የማቅረብ፣
- በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዝርዝር የማወቅና የመጠቀም፤
- ተገቢ የሆነ ድጋፍና እገዛ የማግኘት፤
- ቀልጣፋ አገልግሎት የማግኘት፤
የተገልጋዮች ግዴታዎች
- ሕጎችንና የአሰራር መመሪያዎችን መከተል
- ለሚፈልጉት አገልግሎት የተሟላና ትክክለኛ መረጃ የማቅረብ፣
- ተገልጋዬች አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ
ተፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላት