image
image
image
image
image

ለሸማች ህብረት ስራ ማህበራት አመራሮችና ለዘርፉ ባለሙያዎች ለ4 ተከታታይ ቀን ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ተጠናቀቀ።

ጥቅምት 16, 2017
የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተጫነ አዱኛ በስልጠናው ማጠቃለያ እንደተናገሩት ህብረት ስራ ማህበራት ከመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራር የጸዱና አገልግሎታቸውን በማዘመን የተቋቋሙለትን አላማ በማሳካት የከተማን ነዋሪዎች በኑሮ ውድነትና ገበያን በማረጋጋት ሰፊ አስተዋፆኦ ማበርከት እንዳለባቸው ተናግረዋል:: ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተጫነ አክለውም አሰራሮችን በማስጠበቅና ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ማህበራት ለመፍጠር ሁሉም ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል:: የልደታ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ባዬ ባይሌ በበኩላቸው ስልጠናው በህብረት ስራ ማህበራት መመሪያና ደንብ ቁጥር 170 እና 171/2016 መሰረት በማድረግ የተሻለ ተቋም ለመገንባት የተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል:: አቶ ባዬ አክለውም የተሰጠውን ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር ፈጣን ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰባችንን እርካታ በማሳደግ ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን በመከላከልና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ሁሉም በተሰማራበት ዘርፍ ውጤታማ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል:: የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተሰጠው ስልጠና ለስራቸው አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልፀው በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ ስራ በመስራት ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል::

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች