የልደታ አስተዳደር ህንጻ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁ 403
+251929373929
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ለመልካም አስተዳደር አስተያየት
የመረጃ መሰብስቢያ
ሚዲያ
ዜና | News
Online TV
መጽሄቶች | Magazines
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
ማስታወቂያ
ለማንኛዉም ጥያቄዎ
በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች
የጽ/ቤቱን ሮቦት ይጠይቁ
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ይግቡ
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
መጽሄቶች | Magazine
Online TV
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Web APP
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ይግቡ
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት የፋይናንስ ህብረት ስራ ልማት ቡድን ለቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር አመራሮችና ለወረዳ ቡድን መሪዎች በደንብ ቁጥር 170/2016 ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።
ህዳር 16, 2018
በልደታ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት የፋይናንስ ህብረት ስራ ልማት ቡድን ለቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር አመራሮችና ለወረዳ ቡድን መሪዎች በደንብ ቁጥር 170/2016 ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት እና የቄ /ብ/ህ/ስ/ ማሀበራትን ዓለም አቀፍ በዓልን ለማክበር መድረክ አዘጋጀ። “ሀብረት ስራ ለበለፀገ አለም "
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ፅ/ቤት በመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ተቋማዊ ሪፎርሙ ያመጣቸውን ውጤቶች እና ተግዳሮቶች ከህብረት ስራ ማህበራት እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ
ነሀሴ 24, 2018
በውይይቱም ላይ የመልካም አስተዳደር ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እና የመጡ ውጤቶች እንዲሁም በተቋማዊ ሪፎርም የመጡ ውጤቶች እና ተግዳሮቾች የህብረት ስራ ማህበራት አመራሮች ፣ ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች በተገኙበት በጥልቀት በመወያዩት በቀጣይ በዓላት የሚሆን ግብዓት በማስገባትና ለሸማቹ ለማሰራጨት እየተደረገ ያለውን ዝግጅት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል። ሁሉም ማህበራት የተቋቋሙበትን ዋና አላማ መነሻ በማድረግ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው የጋራ መግባባት መፍጠር ተችሏል ያሉት አቶ ባዬ በተጨማሪም በውይይቱም በቀጣይ የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የአገልግሎት አሠጣጥ መማክርት ጉባኤ አባላትን በመምረጥ የተጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርሙን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በውይይቱ መግባባት ተችሏል በቀጣይ የህብረት ስራ ማህበራት በህብረት ሰርቶ በህብረት ማደግ የሚያስችል አቅም መፍጠር የሚያስችል ተቋማዊ ለውጥ በተግባር እያረጋገጥን መሄድ አለብን በተለይም የህብረተሠቡን ፍላጎት መሠረት ያደረገ አቅርቦት እና ፍላጎትን የሚጣጥም ተግባራትን ማከናወን ይገባል ብለዋል።
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ፅ/ቤት ለመጭው አዲስ አመት በአልን ምክንያት በማድረግ ለበአሉ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ምርቶችን በሸማች የህብረት ስራ ማህበራት በኩል በቂ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገለፀ።
ነሀሴ 29, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ የህብረት ስራ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ባዬ ለመጪው አዲስ አመት ለበአሉ የሚያስፈልጉ የግብርናና ፣የኢንዱስትሪ ምርቶችን እንዲሁም የእንስሣት ተዋፅኦ ምርቶችን በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ በሸማች የህብረት ስራ ማህበራት በኩል በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል ። በሸማች ማህበራት በመጋዘኖች የመሸጫ ሱቆች እና በእሁድ ገቢያዎች እንዲሁም በአሉን ታሣቢ በማድረግ በ10 ወረዳዎች ባዛር በማዘጋጀት ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የህብረት ስራ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ባዬገልፀዋል። በአሉንም ምክንያት በማድረግ በሁሉም የሸማች ማህበራት መጋዝኖች እና የመሸጫ ሱቆች ላይ በቂ የዘይት ምርቶች በማስገባት ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቱ እንደሚቀርብ ገልፀዋል ። የበአላት የፍጆታ ምርት አቅርቦቱ በቀጣይ ቀናቶችም በተጠናከረ አግባብ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንደሚቀርብ የገለፁት አቶ ባዬ አያይዘው ለመጪዎቹ በአላት ለፋጆታ የሚውሉ ግብዓቶችን ከአምራቾች እና ምርት አቅራቢ ዪኔኖች ጋር ጠንካራ የገቢያ ትስስር በመፍጠር ለህብረተሰቡ አስፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑን ሃላፊውም ተናግረዋል ። በዛሬው እለትም ፈሳሽ ዛይት በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ወደ ማህበራቱ የመጋዝኖች እና መሸጫ ሱቆች መግባታቸው ገልጿል። መጪዎቹን በዓል ምክንያት በማድረግ በሁሉም የሸማች ሱቆችና ወፍጮ ቤቶች ፤ ጤፍን ጨምሮ ሀሉንም አይነት የሰብል ምርቶች እንዲሁም እሴት የተጨመረባቸው ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ይቀርባሉ ብለዋል።
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ 21 ሺህ 971 ለሚሆኑ በእንስሳት እርባታ ለተሰማሩ አርቢዎች የእንስሳት መኖ የማቅረብ ስራ ተከናወነ።
መጋቢት 5, 2018
የክ/ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ከህብረት ስራ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ትስስር ለተፈጠረላቸው አርቢዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የእንስሳት መኖ አቅርበዋል። የክ/ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው እንደተናገሩት መኖውን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ መቻሉ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ይጨምራል ብለዋል። በሌማት ቱሩፋት ስራ የከተማዋን ነዋሪዎች ከሸማችነት ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩ ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በዚህም አብዛኛው የከተማው ነዋሪዎች ባላቸው ክፍት ቦታ እንስሳት በማርባት ከራሳቸው አልፈው ለገብያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። አርቢዎች ምርታቸውን በስፋት እንዲያመርቱ ለማስቻል ክ/ከተማው የእንስሳት መኖ አቅርቦት በፋት እያቀረበ ይገኛል በዚህም በዛሬው ዕለት በያዋጣናል እና በትግል ፍሬ ሸማች ህብረት ስራ ማህበር አማካኝነት መኖ እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ገልፀዋል። መኖ እየቀረበ የሚገኘውም ሌላ ቦታ ከሚሸጠው ከ8 መቶ እስከ 1 ሺህ ብር የዋጋ ቅናሽ እንዳለውም ተጠቁሟል።
ዜና | Oduu | News
2ኛው ዙር የህብረት ስራ ማህበራት ሪፎርም ትግበራ ውጤታማ መሆኑን የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የምክር ቤት አመራሮችና አባላት ገለፁ።
ግንቦት 21, 2018
የምክር ቤቱ አመራርና አባላት በልደታ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት በ2ኛው ዙር እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ስራዎችን ጎብኝተዋል። የምክር ቤት አመራርና አባላት በህብረት ስራ ማህበራት እየተከናወነ ያለው ሪፎርም የረጅም ጊዜ የማህበረሰቡን ጥያቄዎች የመለሰ ነው ብለዋል። የህ/ሰራ ማህበራት 2ኛው ዙሪ የሪፎርም ትግበራ ውጤታማና ከዚህ በፊት የነበረውን የተንቀራፈፈ አሰራርና የግብዓት ብክነት ያስቀረ መሆኑን የገለፁት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ባየ ባይሌ ትግበራው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። ኃላፊው አክለውም በሪፎርሙ የተተገበሩ ስራዎች ደረጃቸውን የጠበቁና ሸማቹ ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልፀው በርካታ የስራ እድል እንደተፈጠረባቸውም አብራርተዋል። ሱፐር ማርኬቶች፣ የመዝናኛ ክበቦች፣ የእንጀራ መጋገሪያ እና የተለያዩ ካፌዎች የሪፎርሙ ውጤቶች መሆናቸውን ተገልጿል።
ዜና | Oduu | News
"ጠንካራ ተቋማዊ ሪፎርም ለተቋም ግንባታ መሰረት ነው'' በሚል መሪ ቃል ለጽ/ቤት አመራሮች ፣ለባለሙያዎች እና ለሸማች ማህበራት አመራሮች ስልጠና ተሰጠ ።
ጥቅምት 11, 2018
ስልጠናውን የሚሰጠው የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ማህበር ሲሆን ጽ/ቤቱ በህብረት ስራ ማህበራት መመሪያና ደንብ ቁጥር 170 እና 171/2016 መሰረት በማድረግ እየሰጠ ያለው። የክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባዬ ባይሌ የስልጠናውን ዓላማ ሲገልፁ በሸማች ሪፎርም የተጀመረውን ትግበራ ውጤታማ እንዲሆንና ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች፣ባለሙያዎችና ሸማች ማህበራት በመመሪያና ደንብ ላይ ያላቸው ግንዛቤ ተመጣጣኝ እንዲሆን ለማስቻል ነው ብለዋል። አቶ ባዬ አያይዘው እንደገለፁት ተቋማችን የህዝብ እንደመሆኑ መጠን አገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍ፣አሰራሩን ለማሻሻል በየጊዜው የለውጥ ስራዎች እየሰራን እንገኛለን ያሉ ሲሆን ከእዚህ ስልጠና በኋላም የህብረተሰቡን ፍትሀዊ የሆነ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣የመልካም አስተዳደር ችግርን መቅረፍ፣ የህብረተሰቡን ፍላጎትና አቅርቦት አመጣጥኖ በማቅረብ የኑሮ ውድነትን ማቅለል፣ ማንኛውም በህብረት ስራ ላይ ተጠቃሚ የሚሆን አካል ህግና መብቱን አዉቆ በስርዓት እንዲገለገል ውጤት ይጠበቃል ዓላማው እንዲሳካም ስልጠናውን ተግባራዊ ማድረግና በጋራ መስራት አለብን ብለዋል። ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለ4 ቀን እንደሚቆይና የሚሰጠውን ስልጠና በጥብቅ ዲሲፒል ተከታትሎ ማጠናቀቅ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልጿል።
ዜና | Oduu | News
ተቋማዊ ሪፎርም በመደረጉ የሸማች ማህበራት ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የልደታ ክ/ከተማ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት ገለፀ።
ጥቅምት 1, 2018
ጽ/ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል። የልደታ ክ/ከተማ ም/ሥራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ነፃነት ደረሰ እንደተናገሩት በተቋሙ ሪፎርም በመሠራቱ እና ብልሹ የሆኑ አሰራሮችን በማስወገድ የተሻለ ስራዎችን መሠራቱን ጠቁመው ሸማች ማህበራቱ ለህብረተሰቡ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ በማድረጋቸው የኑሮ ውድነቱን የማቃለል ስራ ሰርተዋል ብለዋል። ወ/ሮ ነፃነት አክለውም የሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት የህብረተሰቡን ችግር ለማቃለል ጉልህ ሚና ስላላቸው የተለያዩ የፍጆታ ዕቃዎችን በተቀመጠላቸው ዋጋ መሠረት ማህበረሰቡን ማገልገል አለባቸው ብለዋል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ባዬ ባይሌ በበኩላቸው በተቋሙ ሪፎርም በመሠራቱና አገልግሎት አሰጣጡ በመዘመኑ በ1ኛ ሩብ ዓመት የተሻለ ስራ መሠራቱን ተናግረው ሸማች ማህበራት የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ በታማኝነት በማገልገል የኑሮ ውድነቱን የማርገብ ስራ እንሰራለን ብለዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በየጊዜው የሚጨምረውን የኑሮ ውድነት ለማርገብ በሩብ ዓመቱ የተሰራው ስራ ጥሩ ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይም በተጠናከረ መልኩ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል። በመጨረሻም በ2016 በጀት አመት የተሻለ የስራ አፈፃፀም ለነበራቸው ወረዳዎች፣ ባለሙያዎች፣ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት እውቅና ተሰጥቷል::
ዜና | Oduu | News
ለሸማች ህብረት ስራ ማህበራት አመራሮችና ለዘርፉ ባለሙያዎች ለ4 ተከታታይ ቀን ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ተጠናቀቀ።
ጥቅምት 16, 2018
የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተጫነ አዱኛ በስልጠናው ማጠቃለያ እንደተናገሩት ህብረት ስራ ማህበራት ከመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራር የጸዱና አገልግሎታቸውን በማዘመን የተቋቋሙለትን አላማ በማሳካት የከተማን ነዋሪዎች በኑሮ ውድነትና ገበያን በማረጋጋት ሰፊ አስተዋፆኦ ማበርከት እንዳለባቸው ተናግረዋል:: ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተጫነ አክለውም አሰራሮችን በማስጠበቅና ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ማህበራት ለመፍጠር ሁሉም ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል:: የልደታ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ባዬ ባይሌ በበኩላቸው ስልጠናው በህብረት ስራ ማህበራት መመሪያና ደንብ ቁጥር 170 እና 171/2016 መሰረት በማድረግ የተሻለ ተቋም ለመገንባት የተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል:: አቶ ባዬ አክለውም የተሰጠውን ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር ፈጣን ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰባችንን እርካታ በማሳደግ ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን በመከላከልና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ሁሉም በተሰማራበት ዘርፍ ውጤታማ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል:: የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተሰጠው ስልጠና ለስራቸው አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልፀው በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ ስራ በመስራት ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል::
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ "ህብረት ስራ ማህበራት ለሀገራዊ ብልፅግና"በሚል መሪ ቃል ለገንዘብ ቁጠባና ብድር ማህበራ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ህዳር 21, 2018
የልደታ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት በህብረት ስራ ማህበራት ደንብ ቁጥር 170/2016 እና 171/2016 ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሰጥቷል። የልደታ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባዬ ባይሌ እንደተናገሩት ልጠናው የተጀመረው የህብረት ስራ ማህበራትን ሪፎርም ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል እንዲሁም ከዚህ ቀደም የነበሩ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ማሻሻል የሚያስችል ነው ብለው በማህበራት ያሉ ብልሹ አሰራሮችን ማስወገድ የሚስችል ነው ብለዋል። ሰልጣኞች በበኩላቸው ስልጠናው በደንቡና መመሪያው ላይ ሰፊ ግንዛቤና ግልፀኝነትን በመፍጠር ተወዳዳሪ እንድንሆን አቅም ፈጥሮልናል ብለዋል።
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ለባለሙያዎችና ለባለድርሻ አካላት በሂሳብ አያያዝ በአጫጭር ጥናትና ፣ በቢዝነስ ፕላን ዙሪያ ስልጠና ሰጠ::
ታህሳስ 4, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ የህብረት ስራ ማህበር ጽ/ቤት ሀላፊ እንደተናገሩት ጽ/ቤቱ በቅርቡ ሪፎርም ያደረገ ተቋም እንደ መሆኑ ስልጠና በመስጠት ሸማች ማህበሩ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና የተሻለ የሒሳብ አያያዝ ላይ ግንዛቤ መፍጠር መቻሉ እንደ ጠንካራ ጎን የሚወሰድ ነው በማለት ሰልጣኞች የሂሳብ አያያዝና ላይ የተሻለ ግንዛቤና ክህሎት ኖሯቸው በተሰማሩበት የስራ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛል በማለት ገልፀዋል። አቶ ባዬ አክለው ስልጠናው የተሻለ ክህሎትና አቅም እንደሚፈጥር እና ስራዎችን አንድ ደረጃ ከፍ አድርገን እንድንሰራ የሚያደርግ ነው በማለት ሰልጣኞችም ከስልጠናው በኋላ የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ሊወጡ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል ወደ ተግባር መለወጥ ይጠበቅባችኋል በማለት ገልፀዋል።
መግቢያ
ስለ_እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
ፎቶግራፎች | Photo Gallery
ቪዲዮዎች | Videos
መግለጫዎች | Press Release
መጽሄቶች | Magazine
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Online TV
Web APP
የዛሬይቱ ልደታ
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ያግኙን
lidetacoop@gmail.com
+251929373929