image
image
image
image
image

ተቋማዊ ሪፎርም በመደረጉ የሸማች ማህበራት ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የልደታ ክ/ከተማ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት ገለፀ።

ጥቅምት 1, 2017
ጽ/ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል። የልደታ ክ/ከተማ ም/ሥራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ነፃነት ደረሰ እንደተናገሩት በተቋሙ ሪፎርም በመሠራቱ እና ብልሹ የሆኑ አሰራሮችን በማስወገድ የተሻለ ስራዎችን መሠራቱን ጠቁመው ሸማች ማህበራቱ ለህብረተሰቡ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ በማድረጋቸው የኑሮ ውድነቱን የማቃለል ስራ ሰርተዋል ብለዋል። ወ/ሮ ነፃነት አክለውም የሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት የህብረተሰቡን ችግር ለማቃለል ጉልህ ሚና ስላላቸው የተለያዩ የፍጆታ ዕቃዎችን በተቀመጠላቸው ዋጋ መሠረት ማህበረሰቡን ማገልገል አለባቸው ብለዋል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ባዬ ባይሌ በበኩላቸው በተቋሙ ሪፎርም በመሠራቱና አገልግሎት አሰጣጡ በመዘመኑ በ1ኛ ሩብ ዓመት የተሻለ ስራ መሠራቱን ተናግረው ሸማች ማህበራት የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ በታማኝነት በማገልገል የኑሮ ውድነቱን የማርገብ ስራ እንሰራለን ብለዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በየጊዜው የሚጨምረውን የኑሮ ውድነት ለማርገብ በሩብ ዓመቱ የተሰራው ስራ ጥሩ ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይም በተጠናከረ መልኩ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል። በመጨረሻም በ2016 በጀት አመት የተሻለ የስራ አፈፃፀም ለነበራቸው ወረዳዎች፣ ባለሙያዎች፣ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት እውቅና ተሰጥቷል::

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች